News News

የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለድርድር በተለዩ ጉዳዮች ተጨማሪ ውይይት በማካሄድ ቅድመ ድርድር ሂደትን አጠናቀቁ

የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለፈው ሳምንት ለድርድር በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ ተጨማሪ ውይይት በማካሄድ የቅድመ ድርድር ሂደቱን ባለፈው ቅዳሜ አጠናቅቀዋል፡፡ ድርድር እንዲካሄድባቸው ከቀረቡ አጀንዳዎች መካከል በአብዛኛዎቹ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ድርድር እንዲካሄድባቸው ስምምነት ከተደረሰባቸው አጀንዳዎች በተጨማሪ በአስቸኳይ የጊዜ አዋጅ አለም አቀፍ የድንበር እና የባህር በር፤ የመሬት ፖሊሲ፣ የህገ መንግስት መሻሻል እንዲሁም የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች የሚሉ አጀንዳዎች ድርድር እንዲደረግባቸው የድርድሩ ተሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል፡፡

Read More

“በተከፈለው መስዋዕትነት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ስርዓት እውን ሆኗል”

29ኛው የትግራይ ሰማዕታት ቀን ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ የአዲስ አበባና አከባቢዋ የህወሓት ታጋዮች ማሕበር ቅርንጫፍ አስተባባሪነት በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡ በዝግጁት ላይ የተገኙት ታጋይ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እለቱ የተለየ መሆኑን በመግለፅ በተከፈለው መስዋዕትነት አምባገነኑን የደርግ ስርዓት በመቀየር በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የትግራይ ህዝብ ወደ ትግል የገባው ወዶ አልነበረም ያሉት ታጋይ ዶ/ር ድብረፅዮን የደርግ መንግስት ሁሉንም አማራጮች የዘጋ አምባገነን በመሆኑ እንኳንስ የብሄር መብት ማክበር ይቅርና በግልም ጭምር ማሰብን የማይፈቅድ አስከፊ ስርዓት ሰለነበረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም በተከፈለው ከባድ መስዋዕትነት ያንን አስከፊ ስርዓት መቀየር ተችሏል ብለዋል፡፡

Read More

የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ የሚደራደሩባቸው አጀንዳዎች ተለዩ

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደት ውይይት ላይ የተጠቃለሉ የጋራ የድርድር ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ በስፋት ከተወያዩ በኋላ የጋራ አቋም በያዙባቸው የድርድር አጀንዳዎች ላይ ለመደራደር የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የፀረ ሽብር አዋጅ፣ የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ፋይናንስና የታክስ ስርዓት ህግ፣ የፍትህ አካላት አደረጃጀት አዋጅና የበጎ አድራጎትና ማህበራት አዋጅ የሚሉ የመደራደሪያ አጀንዳዎችን ያቀረቡ ሲሆን በኢህአዴግ በኩል ከቀረቡ መደራደሪያ አጀንዳዎች መካከል ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውጪ በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል፡፡

Read More

H.E Mr. Tefera Deribew Addressed the BRICS Forum held in China

H.E, Mr. Tefera Deribew, Member of the EPRDF Central Committee, Democratic system Building Coordination Center Rural Politics Coordinating Minister and Head of the EPRDF Secretariat Rural Politics and Organizational Affair addressed his remarks during ongoing BRICS and some developing countries’ Political Parties, Think-tanks and Civil Society Organizations Meeting in June 11, 2017, Fuzhou, China.

Read More

May 28th victory is a victory of all nations, nationalities and peoples of Ethiopia: - Head of EPRDF public and foreign relation

Secretariat of the council of EPRDF said that the May 28th victory down fall of Derg regime is the victory of all nations and nationalities in Ethiopia Comrade Fekadu Tesema; head of EPRDF public and foreign relation who host the panel discussion stated that Ethiopian Federalism has unique features and quite different from other federal systems. According to Comrade Fekadu Ethiopian federalism system is based on heterogeneous tolerance and give emphasis to universal declaration of Human right 1948. In addition the right of individual and group rights as well as minority rights are strongly granted. Many more Fekadu said EPRDF federal system is also focus on guaranty of political and economic rights of nations up to self-determination.

Read More

ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

Pages: 1  2  

portrait of Meles portrait of Meles

ከኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባካሄደው ጥልቅ ግምገማ የድርጅቱን ተሃድሶ በፅኑ መሠረት ላይ ማኖር እና ድርጅቱን በጥልቅ በማደስ ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር ወቅታዊ ጉዳይ በመሆኑ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ከምንጊዜውም በበለጠ አካሄድ አዲስ ድል ለማስመዝገብ ቁርጠኛና ዝግጁ መሆኑን በመገለፅ በተለየ መንፈስ ውይይት በማድረጉ የግምገማ መድረኩን ወቅታዊ ወሳኝ የትግል መድረክ ብሎ በመሰየም በካሄድው ውይይት ታሪካዊ ስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሠርት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 4-10/2009 ዓ.ም በአዳማ በካሄደው ጥልቅ የተሃድሶ ግምገማ የድርጅቱን የ15 ዓመታት የስኬት ጉዞ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች አብይ ምክንያቶች ለመገመገም የወደፊት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡ ባለፉት 15 ዓመታት ከሁሉም በላይ ከድርጅቱ ስኬቶች መካከል በኋላቀረነት እና በድህነት ላይ በተካሄደው ዘመቻ የኦሮሚያ ክልል የገጠሩና የከተማ አካባቢ ብሩህ ተስፋ እንዲለመልም ማድረግ ተችሏል፡፡

Pages: 1  2  3  4  5  

ከኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ከኢህአዴግ ጉባኤ ቀጥሎ ከፍተኛው የስልጣን አካል የሆነው የኢህአዴግ ምክር ቤት ከነሃሴ 18 - 22/2008 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የቀረበውን የ15 አመት የአገራዊ ህዳሴ ጉዞ ግምገማ መነሻ በማድረግ በጥልቀት የገመገመ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በምንገኝበት ወቅት የሚታዩ ልዩ ልዩ የፖለቲካ ዝንባሌዎችንም የሚመለከት ግምገማ አካሂዷል፡፡ 

Pages: 1  2  3  4  5  

Quick Links Quick Links