”ኢትዮዽያውያንና የህዳሴ ግድባቸው”

እነዝህ ወቅታዊ ፁሁፎች የፓርቲው አቋም ናቸው ተብለው አይወሰዱም


ዛሬ ላይ በልማታቸው ቁንጮ ለመሆን የበቁትን ሀገራት ወደ ኋላ መለስ ብለን የቀደመ ታሪካቸውን ስንመለከት በድህነት አረንቋ ውስጥ ተዘፍቀው ይዳክሩ እንደነበሩ መገንዘብ ይቻላል። ድህነት የውርደትን ካባ አስደርቦ በሀፍረትና አንገት በመድፋት ሲያኖራቸው ዘመናት ነጉደዋል። ባስ ሲልም የህዝባቸውን ሉዓላዊነት ማስጠበቅ ተስኗቸው ሀገራዊ ክብራቸውንና ጥቅማቸውን በተደጋጋሚ ላልተገባ የውጭ ተፅዕኖ ድርድር በማቅረብ የህዝቦቻቸውን አንድነት ለፈተና አጋልጠው የቆዩ እንዳሉም ይታወቃል። አሁን በተሻለ የኢኮኖሚ ደረጃ ላይ የሚገኙ ሀገራትና ህዝቦች ብዙዎቹ ትክክለኛ ችግሮቻቸውን ለይተው መንቀሳቀስ በመቻላቸው ግን በሀሳብና በምኞት ደረጃ ሩቅ ይታዩአቸው የነበሩ የእድገት ጭላንጭሎችን ጭራ ተከትለው ያለ  መሰልቸት እና ተስፋ መቁረጥ መራመድ በመቻላቸው ልማታቸው ጎምርቶ ህዝባቸው ተጠቃሚ መሆን እንደሚችል አሳይተዋል።
ይህ ማለት ደግሞ ዛሬ እኛ አፍሪካውያን አህጉራችንና ሀገራችንን በመተው እየተሰደድን ለመኖር የምንጣጣርባቸው ሀገራት  የዛሬ ዕድገታቸቸው፣ የህዝባቸው ስልጣኔና ሰርቶ የመክበር ጉዳይ በአንዳንዶቹ ሀገራት  በአንድ ወቅት ያልነበሩ፣ አይደለም ልንሰደድባቸው ይቅርና ልናስባቸው የማንፈልጋቸው ሀገራትና ህዝቦች ነበሩ። እነዚህ  ሀገራት አሁን የደረሱበት የዕድገት ደረጃ ላይ ከመድረሳቸው በፊት የነበረው ትውልድ ክቡር መሰዕዋትነት ከፍሎ ለአሁኑ ትውልድ የሚሆን እርሾ አኑሮ በማለፉ የዕድገት ጉዞአቸውን የተቃና ማድረግ ችሏል። በጊዜያቸው ልማትን ሲመርጡ ታርዘው፣ ተጠምተው፣ ተጎሳቁለውና አንዳንዴም ከሰውነት ተራ ወጥተው በትጋት ሳይሰለቹ ሌት ቀን ሲሰሩ የወደፊት ህልማቸውን እውን የማድረግ ራዕይ በማነገብ ነበር። ሀገራቸውን ወደ ፊት ማራመድ በሚያስችል የስራ ዘርፍ ሁሉ ይሳተፋሉ፣ ለተሰራው መልካም ስራም ተገቢውን እውቅና ይሰጣሉ፣ ግላዊ ጥቅማቸውና ህይወታቸውንም ለሀገራዊ ክብራቸውና ለህዝባቸው ዘላቂ ጥቅም ተገዥ ያደርጉ ነበር። መንግስቶቻቸው ለሚቀርጿቸው የልማት ትልሞች  አጋርነታቸውን በተግባር በማሳየትም ለጋራ ዕድገትና ብልፅግና ተረባርበዋል።

Pages: 1  2  3  4  5  

 

Ethiopia’s Bid for Peace, Democracy and Development:
 
A Success Story
 
The Ethiopian Peoples’ Revolutionary Democratic Front (EPRDF), along with the peoples of Ethiopia waged a prolonged and bitter struggle to remove a dictatorial fascist regime and bring about democratic order in a new Ethiopia in which human and democratic rights are respected.  Figuring high on the popular movement’s agenda were also the struggle to ensure peace and stability in the country, thereby creating the conditions for the realization of rapid economic development from which all citizens can benefit.
 
Pages: 1  2  3  

የሰራተኛውን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ ፍትሐዊ  እርምጃ

እነዝህ ወቅታዊ ፁሁፎች የፓርቲው አቋም ናቸው ተብለው አይወሰዱም


ሀገራችን የምእተ ዓመቱን የልማት ግብን ለማሳካት እየተረባረበች ነው። በዚህም ቀጣይነት ያለው እድገት በማስመዝገብ ድህነትን ታሪክ ለማድረግ በርትታ እየተጋች ትገኛለች፡፡ በውጤትም በርካታ ድሎችን ማስመዝገብ ችለናል፡፡ ከትናንት ዛሬ በሁለንተናዊ መስክ ለውጦች ደምቀው መታየት ጀምረዋል፡፡ ከሰሜን እስከ ደቡብ፤ ከምስራቅ እስከ ምዕራብ የሃገራችን ክፍል ጠረኑ ሁሉ ልማት ልማት እያለ ነው።
የሀገራችን ዕድገት በሁሉም አካባቢዎች በፍትሐዊነት ወደ ፊት በመገስገስ ላይ ነው። በመዲናችን አዲስ አበባ ብቻ እንኳን ያለውን የልማት እንቅስቃሴ ብንመለከት የሃገራችን የልማት ጉዞ ወዴት እያመራ እንደሆነ ለመመስከር በቂያችን ነው፡፡ የመንገድ ሽፋኑ፣ የቀላል ባቡር ዝርጋታ፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪው፣ የጋራ መኖሪያ ቤቶች መስፋፋት፣ የኢንቨስትመንት እንቅስቃሴው ብቻ በሁሉም መስክ እየተደረገ ያለው የልማት እንቅስቃሴ በእርግጥ ኢትዮጵያ ወዴት እያመራች ነው፤ መድረሻዋስ ምን ይሆናል? ለሚሉት ጠያቄዎች ከቃል በላይ በግልፅ የሚናገሩ እውነታዎች ሆነዋል፡፡
ትናንት ድንጋይ ላይ ቁጭ ብለው ወርቃማ ጊዜአቸው በከንቱ ይባክንባቸው የነበሩ በርካታ የሀገራችን ወጣቶች በተፈጠረላቸው ምቹ ሀገራዊ ሁኔታ ተጠቅመው ሁለመናችንን ወደ ልማት ብለው በመነሳት ታሪክ እየሰሩ ነው። የከተማው ወጣት ከጠባቂነት ተላቆ በጥቃቅንና አነስተኛ የስራ ዘርፍ በመደራጀት ሃብት በማፍራቱ ከራሱ ባሻገር ለሌሎች የስራ እድል በመፍጠር ላይ ይገኛል፡፡ በገጠር አርሶ አደሩ ምርትና ምርታማነቱን በቀጣይነት በማሻሻል ከጎተራው አልፎ ምርቱን ለገበያ እያቀረበ በመምጣቱ ኑሮው በመሻሻል ላይ ነው፡፡ አርሶ አደሩ ከእርሻው የላቀ ተጠቃሚ የሚሆንበት፣ ነጋዴው በዘርፉ ተወዳዳሪ ሆኖ ትርፋማ የሚሆንበት፣ ሰራተኛውም የላቡን የሚቋደስባት የዜጎች እኩል ተጠቃሚነት የሚረጋገጥባት ሀገር ሆናለች ሀገራችን ኢትዮጵያ፡፡ ይህንን እውነታ ደግሞ እኛ ለውጡን እያጣጣምነው ካለነው ከዜጎቿ በተጨማሪ የአለም አቀፉ ማሕበረሰብም እውቅና የሰጠው የአደባባይ ምስጢር ሆኗል፡፡  

Pages: 1  2  3  4  5  6  7  

 

FEW DISILLUSINED DIASPORAS MAY KEEP ON SHOUTING WHILE THE COUNTRY WILL KEEP ON MOVING FORWARD

                By
 
Yohannes Gebresellasie (Ph.d) Canada
 

There are few people in any society who are bestowed with hate, whimsicality and fickleness. That type of lunatic behavior was demonstrated by one Diaspora madcap during the Ethiopian PM’s visit to the USA the other day. It is not worthy mentioning what that individual barked in front of the Ethiopian PM because his preposterous and ludicrous words towards a very respected and admired leader of a great nation and great people can not and does not represent the views of a large majority innocent and peace loving Ethiopian Diasporas or the Ethiopian public at large. On the contrary, a great majority of the Ethiopian Diasporas and the Ethiopian public at large possess a great respect, admiration and love to the person who has spent his whole life serving his country and his people. His services to his people, his country, the whole region, the continent of Africa and even the world at large is well acknowledged, admired and respected by renowned world leaders such as the leader this individual resides. Further, the Ethiopia PM is highly admired by world class intellectuals of high caliber, leaders from across the continent of Africa and most importantly by Ethiopians: the people he dedicated his whole life to their service.

Generally, Ethiopian Diasporas must advocate peace, love, friendship, health and prosperity. That is exactly what Ethiopia needs from them. Further, Ethiopian Diasporas must be a source of knowledge and must advocate stability and prosperity in our era of 21st century and not be a source of embarrassment, disaster and violence.  Very few disillusioned Diasporas have made it their daily duty to provoke violence, anarchy and lawlessness from their sanctuary in North America and Europe. Whereas they enjoy peace, democratic rights and stability within their Diaspora sanctuary, these sources of violence and destruction are trying to poison innocent Diasporas with their lunatic and biased provocations and transfer poisonous messages back home using modern information technology techniques.

Pages: 1  2  3  

በስኬት የታጀበው የልማት ጉዟችን

እነዝህ ወቅታዊ ፁሁፎች የፓርቲው አቋም ናቸው ተብለው አይወሰዱም


የአንድ ሀገር ኢኮኖሚ አደገ ወይም ወደቀ ብሎ ለመፈረጀ በረካታ መመዘኛዎችን መመልክት ግድ ይላል፡፡ የአንድ አገር ኢኮኖሚ የማምረት አቅም ካለፉት ዓመታት ጋር ሲነፃፃር እድገት ካሳየ፣ የዋጋ ግሽበት ወይም የዋጋ ግሽበቱን በመግታት ኢኮኖሚውን ማረጋጋት ከተቻለ  ወይም ካለፉት አመታት ጋር በአንፃራዊነት መሻሻል ካሳየ እና የኢኮኖሚ ግስጋሴው በተነፃፃሪት ወደ ፊት የሚራመድ ከሆነ ኢኮኖሚው እያደገ ነው ማለት ይቻላል። የመንግስት በጀት ሁኔታ፣ የዋጋ ንረት፣ የመንግስት የታክስ አሰባሰብና አፈፃፀም ብቃት፣ የሀገሪቱ የቁጠባ ሁኔታ፣ ወ.ዘ.ተ የመሳሰሉት የማክሮ ኢኮኖሚው አፈፃፀም አመልካቾችም የሚዘለሉ አይደሉም። ፈጣን ኢኮኖሚያዊ እድገት እንደ ጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት እድገት፣ አጠቃላይ የዜጎች የነፍስ ወከፍ ገቢ፣፣ የንግድ ስፋት፣ የውጭ ምንዛሪ ክምችት የመሳሰሉ የኢኮኖሚ መረጃዎችም የአንድ ሀገር ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ማሳያዎች ናቸው፡፡ እንደ አጠቃላይ ግን የኢኮኖሚ እድገቱ ዋጋ የሚኖረው እና ዕድገቱም አወንታዊ ገፅታ የሚላበሰው የዜጎችን ሁሉን አቀፍ ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ከሆነ ብቻ ነው። ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በሀገሪቱ ውስጥ የተመዘገበው እድገት የተረጋጋና ቀጣይነት ያለው ስለመሆኑ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። ከሁሉም በላይ ደግሞ የኢኮኖሚ እድገቱን ጤናማነት፣ ሰፊ የስራ እድል በመፍጠርና ለዜጎች የስራ ዋስትና በመስጠት የኑሮ ሁኔታቸው በቀጣይነት መሻሻሉን ማየት እጅግ ጠቃሚ ይሆናል። እነዚህ ከላይ የጠቀስናቸው ነጥቦች የኢኮኖሚ እድገቱ አመላካቾች ተደርገው መወሰድ የሚችሉ በመሆናቸው ሀገራችን ያለችበትን ሁኔታም እነዚህን አመላካቾች በመጠቀም መዳሰስ እንችላለን።  
አምባገነኑን የደርግ ስርዓት በህዝቦች የተባበረ ክንድ ግብአተ መሬቱ በተፈፀመበት በ1983ዓ.ም የሀገራችን ኢኮኖሚ ባለበት እንኳን መቀጠል ተስኖት ተንገራግጮ የቆመበት ሁኔታ ተፈጥሮ ነበር። አብዛኛው ዜጋ በፍፁም ድህነት ውስጥ የተዘፈቀበትና መሰረታዊ የሚባሉ ማህበራዊ አገልግሎቶች የተስፋ ጭላንጭላቸው የውሃ ሽታ የሆነበት፣ በአጠቃላይ ሀገራችን የድህነት፣ የድንቁርናና የኋላቀርነት ተምሳሌት ተደርጋ የምትወሰድበት ወቅት ነበር የተፈጠረው፡፡
ኢህአዴግ የደርግን ስርዓት ከገረሰሰ በኋላ ኢኮኖሚውን ከኋሊት ጉዞ በማላቀቅ እንዲረጋጋ፣ በሂደትም እንዲያገግም እና ወደ እድገት ጎዳና እንዲሸጋገር ለማድረግ ከፍተኛ ትግል የጠየቀ ውስብስብ ፈተና ነበር የተደቀነበት። የመንግስት አስተዳደርን እና አገሪቱ የምትመራባቸውን ተቋማት ዲሞክራሲያዊ እና ያልተማከሉ በማድረግ፣ ኢኮኖሚውን በገበያ መር ስርዓት እንዲመራ የሚያስችል ፖሊሲ በመቅረፅ፣ በፖሊሲ መዛባት፣ ጦርነትና በተፈጥሮዓዊ ክስተቶች ሳቢያ የተሸመደመደውን ኢኮኖሚ አቅጣጫ ለመቀልበስ የሚያስችሉ ተራማጅ እርምጃዎች በመውሰድ ረገድ ኢህአዴግ ከሽግግሩ ወቅት ጀምሮ በከፍተኛ የኃላፊነት መንፈስ ተንቀሳቅሷል፡፡

Pages: 1  2  3  4  5  6  

 

A REMINDER CALL FOR ETHIOPIAN DIASPORAS ON
 
THE FIRST YEAR INAGURATION OF THE GRAND
 
ETHIOPIAN RENAISSANCE DAM
 
 
BY
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 
 

YOHANNES GEBRESELLASIE (Ph.D) CANADA

Ethiopia has embarked on an ambitions Grand Renaissance Dam project. This ambitious project is achievable because the government and people of Ethiopia have drawn unlimited focus upon all aspects and in all facets for its construction.

Pages: 1  2  3  4