ኢህአዴግ አገር የመምራት ሃላፊነትን ከተረከበ ጊዜ ጀምሮ ከውስጥም ከውጭም የሚነሱ በርካታ ውጣ ውረዶችን ያስተናገደ ድርጅት መሆኑ ይታወቃል፡፡ ከአገራችን ነባራዊ ሁኔታ ጋር የሚጣጣምና የህዝባችንን ሁለንተናዊ መለወጥ ታሳቢ ያደረገ የፖለቲካና ኢኮኖሚ ስርዓት በማራመድ በውጭ ሃይል ተፅእኖ የሚጠመዘዝ ድርጅት አለመሆኑን ገና በጠዋቱ በተግባር ያሳየ ድርጅት ነው፡፡

ከደርግ ውድቀት ማግስት አገራችን የመበታተን ስጋት ውስጥ የነበረችበት ሁኔታ ቢኖርም መላ የሃገሪቱን ህዝቦች በማስተባበርና በብስለት በመምራት ዴሞክራሲያዊ አንድነቷ በፅኑ መሰረት ላይ እየተገነባ እንዲዘልቅ አስችሏል። ህገ መንግስታችን የአንድነታችንና የመከባበራችን ማሰሪያ ውል እንዲሆን በሚያስችል መልኩ በህዝብ ሙሉ ተሳትፎ ተቀርፆ በመፅደቁ ያንን የመበታተን ስጋት ተሻግረን በጋራ ለዘላቂ ለውጥ መረባረብ ጀምረናል።

Pages: 1  2  

በኢህአዴግ እንደገና በመታደስ ዙሪያ በፌዴራል መስሪያ ቤቶች የሚገኙ የድርጅቱ የመካከለኛ አመራር አካላት የሁለት ቀናት ግምገማዊ ስልጠና መድረክ ተካሄደ

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመስብሰቢያ አዳራሽ ከሁሉም የፌዴራል ተቋማት የተውጣጡ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የመካከለኛ አመራር አካላት የኢህአዴግ ምክር ቤት የሀገሪቱን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችንና ድርጅቱ አሁን ላይ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በመገምገም የለያቸውን ስኬቶችንና ውስንነቶችን መሰረት በማድረግ የተላለፈውን እንደገና በጥልቀት የመታደስ ድተርጅታዊ ውሳኔ የተመለከተ የሁለት ቀናት ውይይት አካሄደዋል፡፡

«ወጣቶች የኢትዮጵያ ህዳሴ ባለቤቶች ናቸው»- ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ

‹‹ወጣቱ ትውልድ የህዳሴ ባለቤትና የአዲሲቷ ኢትዮጵያ ገንቢ ነው›› ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም የወጣቶች ተሳታፎና ተጠቃሚነትን መሰረት ባደረገ መልኩ ሁሉም ጥያቄዎች በኢትዮጵያ ህዳሴ ማዕቀፍ ውስጥ ደረጃ በደረጃ ምላሽ የሚያገኙና እያገኙ ያሉ ናቸው ብለዋል፡፡ እስከአሁን በተተገበረው የወጣቶች እድገት ፓኬጅ በገጠርና በከተማ ለበርካታ ወጣቶች የስራ እድል መፈጠሩን የገለጹት ጠቅላይ ሚንስትሩ በቀጣይም ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት፤ ከቴክኒክና ሙያ የተመረቁ ወጣቶችን ጨምሮ በግብርና፤ በአይ ሲ ቲ፤ በገጠር የመሰረተ ልማት ዝርጋታና ጥገና፤ በማዕድን ልማትና በቱሪዝም ዘርፍ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ወጣቶች የስራ እድልና የፋይናንስ ድጋፍ እንደሚመቻች ጠቅሰዋል፡፡

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስትር ኃይለማርያም ደሳለኝ በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ በአሁኑ ወቅት በሀገራችን አንዳንድ አከባቢዎች እየታዩ ያሉ ግጭቶች መንስኤዎች በዝርዝር ያስቀመጡ ሲሆን ኢትዮጵያን አደጋ ላይ የሚጥል ስጋት አለመኖሩንና እዚህም እዚያም በሚታዩ ግጭቶች አገሪቱ ትፈራርሳለች የሚለው ስጋት መሰረተ ቢስ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡ እንደ ጠቅላይ ሚንስትሩ ገለፃ ለእነዚህ ግጭቶች እንደ ዋነኛ ምክንያት የሚጠቀሱ አራት መነሻዎች እንዳሉ አመላክተዋል፡፡

ህብረተሰቡ ያሚያነሳውን ጥያቄ መርህን በተከተለ አግባብ ለመፍታት ጥረት እንደሚደረግ ተገለፀ

አቶ ገዱ በአሁኑ ወቅት በተለይ በጎንደርና አካባቢው የተከሰተው አለመረጋጋት በነዋሪዎቹ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴ ላይ ከፍተኛ ችግር አስከትሏል ብለዋል፡፡ በብዙ መልኩ አርዓያና የቱሪስቶች መዳረሻ የሆነችው ጎንደር ከተማ የንግድና ሌሎች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎች መዳከማቸውን ገልጸዋል፡፡ ህዝቡም በሰላም ወጥቶ በሰላም የመግባቱ ሁኔታ ስጋት ውስጥ ከቶታል ነው ያሉት። ደረጃው ቢለያይም በሌሎች የክልሉ አካባቢዎችም ችግሩ እንዳለ ገልፀው መንግስትና ህዝቡ ይህን መሰል ችግር ከዚህ በላይ ተሸክመው የሚቆዩበት ሁኔታ ላይ አይደሉም ብለዋል። በመሆኑም በክልሉ በጎንደርና በሌሎች አንዳንድ አካባቢዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ወደ መደበኛ ሁኔታ ለመመለስ የሰላሙ ባለቤት የሆነው ህዝብ ከመንግስት ጋር አብሮ እንዲሰራ ርዕሰ መስተዳድሩ አሳስበዋል።

የኢህአዴግ ም/ቤት የ15 አመታት የተሃድሶ ጉዞን መገምገም ጀመረ፡፡

የኢህአዴግ ም/ቤት ከድርጅቱ ጉባኤ ቀጥሎ ከፍተኛው የስልጣን አካል በመሆኑ በኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ በቀረበለት የ15 አመታት የተሃድሶ ጉዞ ግምገማ መነሻነት ጥልቀት ያለው ግምገማ በማካሄድ የሚታዩ ችግሮችን መሰረታዊና ስር ነቀል በሆነ ሁኔታ ለመፍታት የሚያስችሉ ውሳኔዎችን እንደሚያስተላልፍም ይጠበቃል፡፡

ከኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ባካሄደው ጥልቅ ግምገማ የድርጅቱን ተሃድሶ በፅኑ መሠረት ላይ ማኖር እና ድርጅቱን በጥልቅ በማደስ ወደ አዲስ ምዕራፍ ማሸጋገር ወቅታዊ ጉዳይ በመሆኑ መሠረታዊ ለውጥ ለማምጣት ከምንጊዜውም በበለጠ አካሄድ አዲስ ድል ለማስመዝገብ ቁርጠኛና ዝግጁ መሆኑን በመገለፅ በተለየ መንፈስ ውይይት በማድረጉ የግምገማ መድረኩን ወቅታዊ ወሳኝ የትግል መድረክ ብሎ በመሰየም በካሄድው ውይይት ታሪካዊ ስምምነት ላይ መድረሱን ይፋ አድርጓል፡፡

በዚሁ መሠርት የኦህዴድ ማዕከላዊ ኮሚቴ ከመስከረም 4-10/2009 ዓ.ም በአዳማ በካሄደው ጥልቅ የተሃድሶ ግምገማ የድርጅቱን የ15 ዓመታት የስኬት ጉዞ እና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች አብይ ምክንያቶች ለመገመገም የወደፊት አቅጣጫዎችን አስቀምጧል፡፡ ባለፉት 15 ዓመታት ከሁሉም በላይ ከድርጅቱ ስኬቶች መካከል በኋላቀረነት እና በድህነት ላይ በተካሄደው ዘመቻ የኦሮሚያ ክልል የገጠሩና የከተማ አካባቢ ብሩህ ተስፋ እንዲለመልም ማድረግ ተችሏል፡፡

Pages: 1  2  3  4  5  

ከኢህአዴግ ምክር ቤት የተሰጠ መግለጫ

ከኢህአዴግ ጉባኤ ቀጥሎ ከፍተኛው የስልጣን አካል የሆነው የኢህአዴግ ምክር ቤት ከነሃሴ 18 - 22/2008 ዓ.ም ባካሄደው ስብሰባ በስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው የቀረበውን የ15 አመት የአገራዊ ህዳሴ ጉዞ ግምገማ መነሻ በማድረግ በጥልቀት የገመገመ ሲሆን ከዚህ በተጨማሪም በምንገኝበት ወቅት የሚታዩ ልዩ ልዩ የፖለቲካ ዝንባሌዎችንም የሚመለከት ግምገማ አካሂዷል፡፡ 

Pages: 1  2  3  4  5  

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

 

ኢህአዴግ የንድፈ ሃሳብ መፅሔት የሆነችው አዲስ ራዕይ የመጋቢት - ሚያዚያ ዕትም ለአንባቢዎቿ እየቀረበች ነው፡፡ መፅሔቷ ሁለት ርዕሰ ጉዳዮችን በመያዝ ለህትመት የበቃች ሲሆን  እርስዎም እንደተለመደው መፅሔቷን ገዝቶ በማንበብ ግንዛቤዎን ያሳድጉ፡፡ መልካም ንባብ!

Quick Links Quick Links

portrait of Meles portrait of Meles