News News

የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለድርድር በተለዩ ጉዳዮች ተጨማሪ ውይይት በማካሄድ ቅድመ ድርድር ሂደትን አጠናቀቁ

የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለፈው ሳምንት ለድርድር በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ ተጨማሪ ውይይት በማካሄድ የቅድመ ድርድር ሂደቱን ባለፈው ቅዳሜ አጠናቅቀዋል፡፡ ድርድር እንዲካሄድባቸው ከቀረቡ አጀንዳዎች መካከል በአብዛኛዎቹ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ ድርድር እንዲካሄድባቸው ስምምነት ከተደረሰባቸው አጀንዳዎች በተጨማሪ በአስቸኳይ የጊዜ አዋጅ አለም አቀፍ የድንበር እና የባህር በር፤ የመሬት ፖሊሲ፣ የህገ መንግስት መሻሻል እንዲሁም የህሊናና የፖለቲካ እስረኞች የሚሉ አጀንዳዎች ድርድር እንዲደረግባቸው የድርድሩ ተሳታፊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ጠይቀዋል፡፡

Read More

“በተከፈለው መስዋዕትነት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ስርዓት እውን ሆኗል”

29ኛው የትግራይ ሰማዕታት ቀን ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ የአዲስ አበባና አከባቢዋ የህወሓት ታጋዮች ማሕበር ቅርንጫፍ አስተባባሪነት በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡ በዝግጁት ላይ የተገኙት ታጋይ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እለቱ የተለየ መሆኑን በመግለፅ በተከፈለው መስዋዕትነት አምባገነኑን የደርግ ስርዓት በመቀየር በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆኑን ተናግረዋል፡፡ የትግራይ ህዝብ ወደ ትግል የገባው ወዶ አልነበረም ያሉት ታጋይ ዶ/ር ድብረፅዮን የደርግ መንግስት ሁሉንም አማራጮች የዘጋ አምባገነን በመሆኑ እንኳንስ የብሄር መብት ማክበር ይቅርና በግልም ጭምር ማሰብን የማይፈቅድ አስከፊ ስርዓት ሰለነበረ መሆኑን ተናግረዋል፡፡ አያይዘውም በተከፈለው ከባድ መስዋዕትነት ያንን አስከፊ ስርዓት መቀየር ተችሏል ብለዋል፡፡

Read More

የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ የሚደራደሩባቸው አጀንዳዎች ተለዩ

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደት ውይይት ላይ የተጠቃለሉ የጋራ የድርድር ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ በስፋት ከተወያዩ በኋላ የጋራ አቋም በያዙባቸው የድርድር አጀንዳዎች ላይ ለመደራደር የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ የተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች የፀረ ሽብር አዋጅ፣ የመገናኛ ብዙሃንና የመረጃ ነፃነት አዋጅ፣ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ፣ የንግድ፣ ኢንቨስትመንት፣ ፋይናንስና የታክስ ስርዓት ህግ፣ የፍትህ አካላት አደረጃጀት አዋጅና የበጎ አድራጎትና ማህበራት አዋጅ የሚሉ የመደራደሪያ አጀንዳዎችን ያቀረቡ ሲሆን በኢህአዴግ በኩል ከቀረቡ መደራደሪያ አጀንዳዎች መካከል ከአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ውጪ በሌሎች አጀንዳዎች ላይ ለመደራደር ዝግጁ መሆኑን አስታውቋል፡፡

Read More

H.E Mr. Tefera Deribew Addressed the BRICS Forum held in China

H.E, Mr. Tefera Deribew, Member of the EPRDF Central Committee, Democratic system Building Coordination Center Rural Politics Coordinating Minister and Head of the EPRDF Secretariat Rural Politics and Organizational Affair addressed his remarks during ongoing BRICS and some developing countries’ Political Parties, Think-tanks and Civil Society Organizations Meeting in June 11, 2017, Fuzhou, China.

Read More

May 28th victory is a victory of all nations, nationalities and peoples of Ethiopia: - Head of EPRDF public and foreign relation

Secretariat of the council of EPRDF said that the May 28th victory down fall of Derg regime is the victory of all nations and nationalities in Ethiopia Comrade Fekadu Tesema; head of EPRDF public and foreign relation who host the panel discussion stated that Ethiopian Federalism has unique features and quite different from other federal systems. According to Comrade Fekadu Ethiopian federalism system is based on heterogeneous tolerance and give emphasis to universal declaration of Human right 1948. In addition the right of individual and group rights as well as minority rights are strongly granted. Many more Fekadu said EPRDF federal system is also focus on guaranty of political and economic rights of nations up to self-determination.

Read More

THE 26TH COLORFUL CELEBRATION OF GINBOT 20 VICTORY

Ginbot 20 (May 28) marks the downfall of the Dictatorial Derg Regime by the struggle and sacrifice of the people led by the EPRDF for the last time. This 26th anniversary Ginbot 20 will colorfully celebrated under the leading motto ² Ethiopia_ committed to ensuring a Federal System based on equality and equity among peoples!² at national level. The victory day is celebrated by scheduled panel-discussion and other events. Ethiopians were being oppressed by and passed through anti-democratic political systems that neglected diversity in language, religion and culture for ages. A new Democratic System that respects diversity had overthrown that oppressive system and paved the way for the foundation of the democratic one on Ginbot 20,1983 (May 28,1991). As a result this opening of a new chapter, observable economical, political and social achievements have been recorded in the country.

Read More

አገር አቀፍ የሲቪክ ማህበራት የምክክር መድረክ በነገው እለት በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት ይካሄዳል

አገር አቀፍ የሲቪክ ማህበራት የምክክር መድረክ በነገው እለት በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት “የሲቪክ ማህበራትን ተሳትፎ በማጠናከር ቀጣይነት ያለው የልማትና የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን እናረጋግጥ” በሚል መሪ ቃል እንደሚካሄድ በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል የፖለቲካ ፓርቲዎችና ሲቪክ ማህበራት ጉዳዮች አስተባባር የሆኑት አቶ አብዱልአዚዝ መሐመድ ገለፁ፡፡ አቶ አብዱልአዚዝ ዛሬ በኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የጋራ ምክክር መድረኩ ዓላማ የሲቪክ ማህበራትን ተሳትፎ በማጠናከር የሚኖራቸውን ሚና ማጎልበት እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡

Read More

የግንቦት 20 ድል ያስገኛቸው ትሩፋቶች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም፡፡ ብሄሮች፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች ኢትዮጵያዊነት ከውጭ በኃይል የሚጫን ሳይሆን አምነውና ፈቅደው የሚቀበሉት የኩራተቸው ምንጭ መሆኑን አምነው በአገራቸው ልማትና ዕደገት እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመደረጉ ብሄሮች፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች በሙሉ አቅማቸው ፊታቸውን ወደ ልማት እንዲያዞሩ በዚህም አገራችን በፈጣን የዕድገት ምህዋር እንድትገባ ማድረጋው አንዱ የግንቦት ሀያ ትሩፋት ነው፡፡ ደርግ በወደቀበት ወቅት በኢትዮጵያ 17 የመገንጠልን አማራጭ የሚከተሉ የታጠቁ ኃይሎች የነበሩ ሲሆን የግንቦት ሀያ ድል በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ፌደራላዊ አንድነት እንዲመሰረት በማድረጉ የመገንጠል ጥያቄዎች እየከሰሙ ጠጥዋል፡፡ በአዲስቷ ኢትዮጵያ ሁሉም ብሄሮች፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች በአገራቸው ጉዳይ እኩል ያገባቸዋል፣ በአንድነት በሃገራቸው ልማት በመሳተፍ ይገኛሉ፡፡

የግንቦት 20 ድል ‹‹ ትበታተናለች›› የተባለችውን አገር ህዝቦቿ ተፈቃቅደውና ተከባብረው በመሰረቱት ጽኑ አንድነት ወደ ፈጣን አዳጊነት እንድትሸጋገር ብሎም ለዘመናት መገለጫዋን ሆነ የቆየውን ድህነትና ኃላቀርነት ቀስ በቀስ እንዲናድ አስችሏል፡፡ የአንደኛው የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን የተመዘገበው ፈጣን ዕድገት ብቻ የአገራችን ኢኮኖሚ በመጠኑ ግዙፍ ከሚባሉ ጥቂት የአፍሪካ አገራት መካከል እንዲጠቀስ ያስቻለ ነው፡፡ ይህም ለቀጣይ ዕድገት ተጨማሪ አቅም መፍጠር እንዳስቻለ ታምኖበታል፡፡ በዚህም ዓመታዊ አማካይ የነፍስ-ወከፍ ገቢ በ2002 ከነበረበት 377 የአሜሪካን ዶላር በ2007 መጨረሻ ወደ 691 የአሜሪካን ዶላር አድጓል፡፡ ይህ ባለፉት አምስት ዓመታት የተመዘገበው ፈጣን የነፍስ ወከፍ ገቢ በፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት፣ ማህበራዊ ልማት እና የአደጋ ተጋላጭነትን በመቋቋም አቅም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ከተደረገ በ2017 ዓ.ም ሀገራችንን መካከለኛ ገቢ ካላቸው ሀገሮች ተርታ ለማሰለፍ የተቀመጠውን ሀገራዊ ራዕይ ለማሳካት የሚያስችል ነው፡፡

ፈጣን ዕድገቱ የዜጐችን ተጠቃሚነት ያረጋገጠ በመሆኑ ፋይዳው ከፍ ያለ ነው፡፡ ዕድገቱ ሠፊ መሠረት ያለው ነው፡፡ አብዛኛው የአገራችን ሕዝቦች ከተሠማሩበት ከግብርና ዘርፍ የመነጨ በመሆኑ አብዛኛውን ሕዝብ ተጠቃሚ ያደረገ እንደሆነ ጥናቶች ያሳያሉ፡፡ የአገራችን የድህነት መጣኔ በ1997 የበጀት ዓመት 38.7 በመቶ የነበረ ሲሆን በ2003 የበጀት ዓመት በተካሄደ ተመሳሳይ ጥናት ይህ መጣኔ ወደ 29.6 በመቶ ዝቅ ብሏል፡፡ ጥናቱ የድህነት መጣኔው በገጠርም በከተማም መቀነሱን አመላክቷል፡፡ በ2007 በጀት ዓመት መጨረሻ የድህነት መጣኔው ወደ 23.4 በመቶ ገደማ ዝቅ ሊል እንደሚችል ተገምቷል፡፡ ይህም ድህነትን በግማሽ መቀነስ የሚለው የምዕተ ዓመቱ የልማት ግብ ማሳካት ያስቻለን አፈፃፀም እንደሆነ ይታመናል፡፡

 

 

Amharic English