ዜና ዜና

ብአዴን ከዴሞክራሲያዊ ድርጅቶች ጋር ያለውን አንድነት በማጠናከር ለበለጠ ድል እንደሚተጋ አስታወቀ

የብሄረ አማራ ዴሞክረሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) ከሌሎች ዴሞክራሲ ድርጅቶችና የለውጥ ኃይሎች ጋር ያለውን አንድነት በማጠናከር በሁሉም መስኮች የተጀመሩ ለውጦችን ከዳር ለማድረስ ጠንክሮ እንደሚሰራ የድርጅቱ ሊቀ መንበርና የኢፌዴሪ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ጓድ ደመቀ መኮነን አስታወቀ፡፡ ኢህዴን/ብአዴን የተመሰረተበት 37ኛ ዓመት የምስረታ በዓል ነባር ታጋዮች፣ የድርጅቱ አባላትና ደጋፊዎች በተገኙበት

ተጨማሪ ያንብቡ…

የብሔረ አማራ ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ(ብአዴን) 37ኛ አመት የምስረታ ተከበረ

‹‹ህዝባዊነትና የዓላማ ፅናት ለዴሞክራሲያዊ አንድነት›› በሚል መሪ ቃል በመከበር ላይ የሚገኘው 37ኛው የኢህዴን/ብአዴን የምስረታ በዓል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመሰብሰብያ አደራሽ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት ተከብሯል፡፡ በበዓሉ ላይ የኢህአዴግ ጽህፈት ቤት፣ የዴሞክራሲ ተቋማት፣ የሜጋ፣ ዋልታና ፋና ሰራተኞችና አመራሮች የተገኙ ሲሆን በዓሉም በፓናል ወይይትና በሌሎች ዝግጅቶች ነው የተከበረው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ፓርቲዎቹ በምርጫ ህጉ አዋጅ ላይ ያካሄዱትን ድርድር አጠናቀቁ

አገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ህጉ አዋጅ ላይ ሲያካሂዱት የቆየው ድርድር ተጠናቀቀ። የ11ዱ ተዳራዳሪ ፓርቲዎች ጥምረት 'ምርጫ ቦርድ' የሚለው ስያሜ ወደ 'ምርጫ ኮሚሽን' እስካልተቀየረ በሚል ለሁለት ቀናት ምንም ሃሳብ ባለመስጠት ድርድሩን በታዛቢነት ተከታትሏል። ኢህአዴግ፣ ኢራፓ፣ የገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ፣ መኢብንና መኢዴፓ ምርጫ ቦርድ የሚለው ስያሜ ሳይለወጥ በአዋጁ ይዘት፣

ተጨማሪ ያንብቡ…

ኢህአዴግና ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ አዋጅ ማሻሻያ ላይ ተደራደሩ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እና አራት ሀገር አቀፍ ተደራዳሪ ፓርቲዎች በምርጫ ቦርድ አዋጅ ዝርዝር ማሻሽያ አንቀፆች ላይ ተደራደሩ። ኢሕአዴግ፣ ኢራፓ፣ የገዳ ሥርዓት አራማጅ ፓርቲ፣ መኢብንና መኢዴፓ ህዳር 5 ቀን 2010ዓ.ም በተካሄደው የድርድር መድረክ የምርጫ ቦርዱ አዋጅ 532/99 ከ1 እስከ 61 ያሉት አንቀፆች ላይ የተደራደሩ ሲሆን፤ በቀጣይ ከ62 እስከ 111 ባሉት አንቀፆች ላይ ለመደራደር ዕቅድ ይዘዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ…