ዜና ዜና

የኢህአዴግ ወጣቶች ሊግ 3ኛውን መደበኛ ጉባኤውን ከነገ ጀምሮ ያካሄዳል

‹‹በወጣቶች የላቀ ተሳትፎና ተጠቃሚነት የህዳሴ ጉዛችንን እናፋጥናለን›› በሚል መሪ ቃል ለሶስት ቀናት የሚካሄደው ይህ ጉባኤ ነገ በጠቅላይ ሚንስትር ጽ/ቤት የመሰብሰብያ አዳራሽ በሚደረግ የመክፈቻ ስነ ስርዓት በይፋ ይጀመራል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የሊጉ አመራርና የኦዲትና ቁጥጥር ኮሚሽን አባላትን በመምረጥ ተጠናቀቀ

በጉባኤው ማጠናቀቂያ ላይ ተገኝተው ለጉበኤያተኛው መልዕክት ያስተላለፉት የጠቅላይ ሚንስትሩ የአደረጃጀት አማካሪ ሚንስትርና የኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ ጓድ ከበደ ጫኔ በደርግ ላይ በተካሄደው ትግል ኢህአዴግን ለድል ያበቃው ለሴቶች፤ ለአርሶ አደሮች፤ ለወጣቶችና ለሌሎች ማህበራዊ መሰረቶች ያለው ውግንና መሆኑን ጠቅሰው አደረጃጀቶች የማህበራዊ መሰረቶቹን ጥቅም ለማረጋገጥ ግንባር ቀደም ሆነው መንቀሳቀስ ይገባቸዋል ብለዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ 3ኛ መደበኛ ጉባኤ የባለፉት ዓመታት አፈጻጸምን በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን አስቀመጠ

የሴቶች ተሳትፎና ተጠቃሚነት በየዘርፉ ለማሳደግ በቀጣይም በሊጉ የተጀመሩ የውስጠ ድርጅትና የፖለቲካ፤ የመልካም አስተዳደርና የዴሞክራሲ ተግባራት ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ጉባኤው አቅጣጫ አስቀምጧል፡፡ በ2ኛው እድገትና ትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም፤ በቁጠባ፤ ለታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ የሚደረገው ድጋፍ፤ የልማት ሰራዊት ግንባታና የስራ አጥነት ችግሮችን መፍታት ዋነኛ የትኩረት ጉዳዮች እንደሆኑ ጉባኤው አጽንኦት ሰጥቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የህዳሴ ጉዟችንን ለማፋጠን የሊጉ አባላት ሚና ከፍተኛ መሆኑ ተገለጸ

በግንቦት 20 የተበሰረውን ድል ተከትሎ በኢህአዴግ የሚመራው የኢፌዴሪ መንግስት የሴቶችን ተጠቃሚነትና ተሳትፎ ለማረጋገጥ መጠነ ሰፊ የህግና የፖሊሲ ማዕቀፎች ተዘጋጅተው መተግበራቸውን ጓድ ኃይለማርያም ደሳለኝ ጠቅሰው የኢህአዴግ ሴቶች ሊግ መመስረት ሴቶች በተደራጃ አኳኋን እንዲንቀሳቀሱና አቅማቸውን እንዲገነቡ አስችሏቸዋል ብለዋል፡፡ ሴቶች የህዳሴ ጉዟችንን ለማፋጠን ጉልህ ሚና እንዳላቸው የጠቆሙት ጓድ ኃይለማርያም ኪራይሰብሳቢነትና ብልሹ አሰራርን ለመግታት የተጀመረውን ትግል አጠናክረው እንዲቀጥሉ ለሊጉ አባላት ጥሪ አቅርበዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…