ዜና ዜና

ሀገር አቀፍ ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች በምርጫ ስርዓት ላይ ተስማሙ

ላለፉት ዙሮች በምርጫ ስርዓት እንዲሁም በምርጫ ቦርድ ስያሜና አወቃቀር ዙሪያ ሲደራደሩ የቆዩት ኢህአዴግና አብዛኞቹ ሀገር አቀፍ ተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስርዓቱ ቅይጥ ትይዩ እንዲሆን ተስማምተዋል፡፡ የምርጫ ስርዓቱ 20/80 ቅይጥ ትይዩ መሆኑ የሀገራችንን ነበራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ያማስገባ ስርዓትና ሳይንሳዊ መሰረት ያለው ሲሆን የባከኑ ድምጾች የሚሰበሰቡበት እንዲሁም የተለያዩ ማህበራዊ መሰረቶች የሚወከሉበት መሆኑን አብዛኞቹ ፓርቲዎች ተስማምተውበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኦሮሞ ህዝብ ዴሞክራሲያዊ ድርጅት/ኦህዴድ/ 7ኛው ድርጅታዊ ኮንፈረንስ ተጠናቀቀ

ከጥቅምት 19 ቀን 2010 ዓ.ም ጀምሮ በአዳማ አባገዳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ሲካሄድ የቆየው የኦህዴድ 7ኛ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ ዛሬ ተጠናቅቋል፡፡ ኮንፈረንሱ የህዝብ አብሮ መኖርና አንድነትን ለማጠናከር የመሪ ድርጅት የኦህዴድ እና የኦሮሞ ህዝብ ሚናና ህብረ-ብሔራዊ ስርዓት ዙሪያ በጥልቀት መክሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ፓርቲዎች በቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓትና የምርጫ ቦርድ አወቃቀር እና ስያሜ ዙሪያ ድርድር አካሄዱ፡፡

አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በዛሬው እለት ባካሄዱት ድርድር በቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓትና የምርጫ ቦርድ አወቃቀር እና ስያሜን በተመለከቱ አጀንዳዎች ላይ ድርድር ያካሄዱ ሲሆን ኢህአዴግ ከተፎካካሪ ፓርቲዎች የቀረበውን የማሻሻያ ሃሳብ ተቀብሏል፡፡ በዚህም የምርጫ ስርዓቱን በተመለከተ 80 በመቶ ለአብላጫ ድምጽ ቀሪውን 20 በመቶ ለተመጣጣኝ ውክልና ለሁለቱም ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ሥርዓት ተግባራዊ ቢደረግ ይበልጥ የዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታውን ለማስፋትና የዜጎች ድምጽ እንዲወከል ያስችላል ሲል ተደራድሯል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ድርጅታችን ቀን ከሌት የሚለፋው የህዝባችንን ፍላጎት ለማርካት ነው - አቶ ለማ መገርሳ

*የኦህዴድ 7ኛ ድርጅታዊ ኮንፈረንስ አዳማ በሚገኘው አባገዳ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ዛሬ በይፋ ተከፍቷል፡፡ በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ ላይ የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ለማ መገርሳ የክልሉ መሪ ድርጅት ኦህዴድ የህዝቡን ጥቅም ለማስከበር በተግዳሮቶች ሳይበገር የታገለና ታሪክ የማይረሳቸውን አንጸባራቂ ድሎች ያስመዘገበ ድርጅት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ከድሎቹ በሻገር በትግል ሂደት የተፈጠሩ ክፈተቶችና ስህተቶችን በማረም ድርጅቱ የህዝቡን ጥያቄ ለመመለስ በአሁኑ ወቅት ከፍተኛ ጥረት እያደረገ እንደሚገኝም ጠቁመዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…