ዜና ዜና

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የድርጅትና የመንግስት ስራዎች የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት አፈጻጸምን ገመገመ

የኢህአዴግ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የድርጅትና የመንግስት ስራዎች የዝግጅት ምዕራፍ ተግባራት አፈጻጸምን ገመገመ የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር(ኢህአዴግ) ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ጥቅምት 22 እና 23 ቀን 2008 ዓም ባካሄደው መደበኛ ስብሰባው የድርጅትና የመንግስት ስራዎች የዝግጅት ምዕራፍ አፈጻጸም ግምግሟል፡፡ በ10ኛ የድርጅቱ ጉባኤ የተቀመጡ ውሳኔዎችንና አቅጣጫዎች በማካተት ዳብሮ የተዘጋጀውን የ2008 የድርጅትና የመንግስት እቅድና የመልካም አስተዳደር የንቅናቄ እቅድ ላይም ተወያይቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የብአዴን/ኢህአዴግ 35ኛ የምስረታ በዓልን አስመልክቶ ከምሁራን ጋር የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል

የብአዴን/ኢህአዴግ 35ኛ የምስረታ በዓልን አስመልክቶ ከምሁራን ጋር የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል በመጪው ህዳር 11 የሚከበረውን የድርጅቱን 35ኛ የምስረታ በዓል ምክንያት በማድረግ ከአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፤ ከሲቪል ሰርቪስና ከኮተቤ ዩኒቨርሲቲ ኮሌጅ የተወጣጡ ምሁራን የታደሙበት የምክክር መድረክ እየተካሄደ ይገኛል፡፡ የኢፌዴሪ ም/ጠ/ሚኒስትርና የብአዴን/ኢህአዴግ ሊቀመንበር ጓድ ደመቀ መኮንን መሪነት እየተካሄደ ባለው መድረክ የብአዴን/ኢህአዴግ የትግል ታሪክና በዴሞክራሲያዊ ብሔርተኝነት ዙሪያ የመነሻ ጹሁፍ ቀርቧል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኢህዴን/ብአዴን የትጥቅ ትግል ማዕከላት የነበሩ ቦታዎች ጉብኝት ተጠናቀቀ

የኢህዴን/ብአዴን የትጥቅ ትግል ማዕከላት የነበሩ ቦታዎች ጉብኝት ተጠናቀቀ * ጉብኝቱ የጋዜጠኞችና የአርቲስቶችን ቀልብ የገዛ እንደነበረም ተጠቁሟል በመጪው ህዳር 11 የሚከበረውን የብአዴን/ኢህአዴግ 35ኛ ዓመት የምስረታ በዓልን ምክንያት በማድረግ ‹‹የጥበብ ጉዞ›› በሚል ርዕስ የጋዜጠኞችና የአርቲስቶች ልዑካን ቡድን ላለፉት 10 ቀናት የድርጅቱ የትጥቅ ጥግል ማዕከላት የነበሩ ቦታዎችንና የኢህዴን/ብአዴን መጠንሰሻና ትግሉን ሲያካሂድበት የነበሩ በርካታ ቦታዎችን ጎበኝቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ እቅድ ዙሪያ የተደረገው ውይይት በሰኬት ተጠናቀቀ

ከተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሁለተኛው የእድገትና ትራንስፎርሜሽን ረቂቅ እቅድ ዙሪያ የተደረገው ውይይት በሰኬት ተጠናቀቀ * ፓርቲዎቹ ግብዓት ይሆኗሉ ያሏቸውን ሃሳቦች ሰንዝረዋል ኢህአዴግ 19 ከሚሆኑ የአገራችን ተቃዋሚ ፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በመጀመሪያው ምዕራፍ የእድገትናት ትራንስፎርሜሽን እቅድ እንዲሁም በሁለተኛው ምዕራፍ ረቂቅ እቅድ ዙሪያ ለሁለት ቀናት በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የአፍሪካ የኢኮኖሚክ ኮሚሽን የስብሰባ አዳራሽ (ኢሲኤ) ያካሄደው ውይይት በስኬት ተጠናቋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…