ዜና ዜና

ከኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር ኢህአዴግ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ከጥቅምት 18-19/2010 ዓ.ም ድረስ በጥልቀት የመታደስ ንቅናቄ የደረሰበት ደረጃ እና ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታን በዝርዝር የገመገመበትን ስብሰባ አካሂዷል፡፡ ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴው ባለፈው ጳጉሜ የተሰበሰበው የኢህአዴግ ምክር ቤት የገመገማቸውንና የወሰናቸውን ውሳኔዎችም በመፈተሽ የተጀመረው የጥልቅ ተሃድሶ እንቅስቃሴ አበረታች ነበር ተጠናክሮ መቀጠል ይገባዋል ያለው የምክር ቤቱ ውሳኔ የደረሰትን ደረጃ ገምግሟል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

አስራ አምስት ተደራዳሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ስርዓቱ ቅይጥ ትይዩ እንዲሆን ተስማሙ።

ኢህአዴግን ጨምሮ 16 አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ህግ 532/99 በሚመለከት አምስተኛ ድርድራቸውን ዛሬ አካሄደዋል። በድርድሩ አስራ አራት ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎች ገዢው ፓርቲ ያቀረበው የአብላጫና ተመጣጣኝ የምርጫ ስርዓት /ቅይጥ ትይዩ/ በምርጫ ህጉ ይካተት የሚለውን ሃሳብ ተቀብለዋል። የኢትዮጵያ ራዕይ ፓርቲ (ኢራፓ) በበኩሉ የምርጫ ህጉ ሙሉ ተመጣጣኝ እንዲሆንና ይህ መሆን ካልቻለ ደግሞ የነበረው የአብላጫ ድምፅ ስርዓት እንዲቀጥል አቋም ይዟል።

ተጨማሪ ያንብቡ…

አገር አቀፍ ተደራዳሪ ፓርቲዎች በቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርዓት አማራጭ ሀሳብ ላይ በጥልቀት ለመወያየት በቀነ ቀጠሮ ተለያዩ

አገር አቀፍ ተደራዳሪ ፓርቲዎች ኢህአዴግ ባቀረበው ቅይጥ ትይዩ የምርጫ ስርዓት አማራጭ ሀሳብ ላይ ተመካክረው ለመምጣትና በጥልቀት ለመወያየት ተጨማሪ ቀጠሮ ወስደው ተለያዩ። ባለፈው ውይይት ከቆመበት የቀጠለው አገር አቀፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር በዛሬው ውሎው የአገሪቷን የምርጫ ስርዓት ለማሻሻል በሚያስችላቸው ነጥብ ላይ መክረዋል። በዚህም በአሁኑ ወቅት አገሪቷ የምትከተለውን የአብላጫ ድምጽ የምርጫ ስርዓት በሌላ ለመተካት የተለያዩ አማራጮችን በማቅረብ ረዘም ያለ ክርክርና ውይይት አካሂደዋል። በቀጣይ አገሪቷ መከተል ያለባት የምርጫ ስርዓት እንደቀድሞው "የአብላጫ ድምጽ፣ የሙሉ ተመጣጣኝ ውክልና /ፕሮፕርሽናል/ ወይስ ሁለቱንም ያማከለ ቅይጥ ስርዓት ይሁን?" የሚለው ፓርቲዎችን ሲያከራክር የቆየ ጉዳይ ነው።

ተጨማሪ ያንብቡ…

10ኛው የሰንደቅ ዓላማ በዓል በድምቀት ተከበረ

10ኛው የሰንደቅ አላማ ቀን “ራዕይ ሰንቀናል፤ለላቀ ድል ተነስተናል” በሚል መሪ ቃል በድምቀት ተከብሯል፡፡ በአዲስ አበባ ስታዲዬም በተከበረው በዓል ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ንግግር ያደረጉት የኢፌድሪ ፕሬዝዳንት ዶ/ር ሙላቱ ተሾመ ሰንደቅ አላማ የኢትዮጵያ ብሄር ብሄረሰቦችና ህዝቦች ዘመን ተሻጋሪ ትግል ያስገኘው ውጤት መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሰንደቅ አላማ በመፈቃቀድ ላይ ለተመሰረተው ዴሞክራሲያዊ አንድነት የቃል ኪዳን አርማ መሆኑን ጠቅሰዋል። ላለፉት 10 ዓመታት ተግባራዊ በተደረጉ የተለጠጡ የልማት ዕቅዶች ለመተግበር ርብርብ ሲደረግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ በአለማቀፍ መድረኮች ላይም ያ ላትሚና እያደገ መምጣቱን ፕሬዝዳንቱ አመልክተዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…