ዜና ዜና

ኢህአዴግና ሲፒሲ የፓርቲ ለፓርቲና በሀገር ደረጃ ያላቸውን ግንኙነት ይበልጥ ለማሳደግ እንደሚሰሩ ገለጸ

የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) እና የቻይና ኮሙዩኒስት ፓርቲ (ሲፒሲ) የሁለትሽ ግንኙነታቸውንና እና በሚመሯቸው ሁለት ሀገራት እንዲሁም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነታቸውን ወደ ላቀ ደረጃ ለማድረስ እንደሚሰሩ ገለጹ፡፡ በኢትዮጵያ ይፋዊ የስራ ጉብኝት በማድረግ ላይ የሚገኙት የሲፒሲ አለም አቀፍ ዲፓርትመንት ምክትል ሚኒስትር ሹ ሊዩ ፒንግ ከኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ውይይት አድርገዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በፖርቲዎች የምዝገባ አዋጅ ላይ ስምምነት ላይ ደረሱ

ባለፉት ሳምንታት በፓርቲዎች ምዝገባ አዋጅ ላይ ድርድር ሲያደርጉ የቆዩት አገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ስምምነት ላይ መድረሳቸውን የድርድር ሂደቱ ሚድያ ኮሚቴ በዛሬው ዕለት በሰጠው መግለጫ ላይ አመልክቷል፡፡ ኮሚቴው የፖለቲካ ፓርቲዎች አዋጅ ምዝገባን በማደናቀፍ የመድበለ ፓርቲ ሥርዓቱ ወደ ፊት እንዳይሄድ የሚያደርጉ ጉዳዮች ካሉ እንዲፈተሸ መደረጉን ተመልክቷል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ የጻፋቸው ሰነዶችን ለማሳተም ዝግጅት ተጠናቅቋል - ወ/ሮ አዜብ መስፍን

የታላቁ መሪ መለስ ዜናዊ 5ኛ ዓመት የመታሰቢያ ቀንን ምክንያት በማድረግ አስተምህሮቶቹን ለማስቀጠል በአቶ መለስ የተጻፉ ሰነዶች እንደሚታተሙ የመለስ ፋውንዴሽን ፕሬዚዳንት ወ/ሮ አዜብ መስፍን ገለጹ፡፡ የመታሰቢያ ቀኑን አከባበር አስመልክተው ወ/ሮ አዜብ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የዴሞክራሲያዊ አስተሳሰብን ጨምሮ በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ አቶ መለስ የጻፏቸው ሰነዶች ተሰብስበው ለህትመት መዘጋጀታቸውን ገልጸዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

ድርድሩ የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱን ለማጠናከር ጉልህ ድርሻ አለው - አምባሳደር ደግፌ ቡላ

በኢህአዴግ እና ሀገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች መካከል እየተካሄደ የሚገኘው ድርድር የመድብለ ፓርቲ ስርዓቱን ለማጠናከር ጉልህ ድርሻ እንዳለው በኢህአዴግ ም/ቤት ጽ/ቤት የፖለቲካ ፓርቲዎችና የሲቪክ ማህበራት ዘርፍ ዋና አስተባባሪ አምባሳደር ደግፌ ቡላ ገለጹ፡፡ በኢህአዴግ ሃሳብ አቅራቢነት የተጀመረው የፖለቲካ ፓርቲዎች ድርድር የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት የአፈጻጸም ጉድለቶችን ለማረምና መሻሻል የሚገባቸውን ህጎች የማሻሻል ዓላማ ያለው መሆኑንም ጠቅሰዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…