ዜና ዜና

የግንቦት 20 ድል ‹‹ ትበታተናለች›› የተባለችውን አገር ህዝቦቿ ተፈቃቅደውና ተከባብረው በመሰረቱት ጽኑ አንድነት ወደ ፈጣን አዳጊነት እንድትሸጋገር ብሎም ለዘመናት መገለጫዋን ሆነ የቆየውን ድህነትና ኃላቀርነት ቀስ በቀስ እንዲናድ አስችሏል፡፡

የግንቦት 20 ድል ያስገኛቸው ትሩፋቶች ተዘርዝረው የሚያልቁ አይደሉም፡፡ ብሄሮች፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች ኢትዮጵያዊነት ከውጭ በኃይል የሚጫን ሳይሆን አምነውና ፈቅደው የሚቀበሉት የኩራተቸው ምንጭ መሆኑን አምነው በአገራቸው ልማትና ዕደገት እኩል ተሳታፊና ተጠቃሚ እንዲሆኑ በመደረጉ ብሄሮች፣ ብሄረ ሰቦችና ህዝቦች በሙሉ አቅማቸው ፊታቸውን ወደ ልማት እንዲያዞሩ በዚህም አገራችን በፈጣን የዕድገት ምህዋር እንድትገባ ማድረጋው አንዱ የግንቦት ሀያ ትሩፋት ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የፌዴራል መንግስት የ2010 በጀት 320 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር ሆኖ ፀደቀ

የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው መደበኛ ስብሰባ የፌዴራል መንግስት የ2010 በጀት 320 ቢሊዮን 803 ሚሊዮን 602 ሺ 160 ብር በጀቱ በምክር ቤት አባላቱና በህዝብ አስተያየት መስጫ መድረኮች ተመከሮበትና አስፈላጊውን ሂደት አልፎ በሙሉ ድምጽ ጸድቋል፡፡ በጀቱ ከ2009 በጀት ከነበረው 274 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ጋር ሲነጻጸር በዘጠኝ ነጥብ ስድስት በመቶ ብልጫ አለው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የኦሮሚያ ክልል በአዲስ አበባ ከተማ ላይ ያለውን ህገ-መንግሥታዊ ልዩ ጥቅም አስመልክቶ የቀረበ መግለጫ፣

የኢትዮጵያ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ሰፊ ውይይት ካካሄዱበት በኋላ በተወካዮቻቸው አማካይነት ያፀደቁት ህገ-መንግሥት የሁሉንም ሕዝቦች መብቶችና ጥቅምች የሚያስጠብቅ ነው፡፡ ህገ-መንግሥቱም የኢትዮጵያ ብሔሮች፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች የቃል-ኪዳን ሰነድ ሲሆን ዓላማውም በሕዝቦች መፈቃቀድና ፍላጎት እንዲሁም ዴሞክራሲያዊ አንድነት ለማጎልበት እንዲቻል በጋራ ያፈሯቸው እሴቶችና ሃብቶች እንዲሁም ትስስሮች እንዳሏቸው በማመን- በታሪካቸው ሂደት ውስጥ ያጎለበቷቸውን የጋራ ጉዳዮች ይበልጥ ለማበልፀግና የተዛቡ ግንኙነቶችንም በማረም አንድ ጠንካራ የጋራ ኢኮኖሚያዊ ማህበረሰብ እና የጋራ ፖለቲካዊ ማህበረሰብ ለመገንባትና ለማጠናከር የታለመ ነው፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ለድርድር በተለዩ ጉዳዮች ተጨማሪ ውይይት በማካሄድ ቅድመ ድርድር ሂደትን አጠናቀቁ

የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች ባለፈው ሳምንት ለድርድር በተመረጡ አጀንዳዎች ላይ ተጨማሪ ውይይት በማካሄድ የቅድመ ድርድር ሂደቱን ባለፈው ቅዳሜ አጠናቅቀዋል፡፡ ድርድር እንዲካሄድባቸው ከቀረቡ አጀንዳዎች መካከል በአብዛኛዎቹ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…