ዜና ዜና

“በተከፈለው መስዋዕትነት በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ስርዓት እውን ሆኗል”

29ኛው የትግራይ ሰማዕታት ቀን ዛሬ በሚሊኒየም አዳራሽ የአዲስ አበባና አከባቢዋ የህወሓት ታጋዮች ማሕበር ቅርንጫፍ አስተባባሪነት በታላቅ ድምቀት ተከበረ፡፡ በዝግጁት ላይ የተገኙት ታጋይ ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል እለቱ የተለየ መሆኑን በመግለፅ በተከፈለው መስዋዕትነት አምባገነኑን የደርግ ስርዓት በመቀየር በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት እውን መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የአገር አቀፍ የፖለቲካ ፓርቲዎች በቀጣይ የሚደራደሩባቸው አጀንዳዎች ተለዩ

የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ዛሬ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ባካሄደት ውይይት ላይ የተጠቃለሉ የጋራ የድርድር ረቂቅ አጀንዳዎች ላይ በስፋት ከተወያዩ በኋላ የጋራ አቋም በያዙባቸው የድርድር አጀንዳዎች ላይ ለመደራደር የጋራ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

የገዳ ስርዓት የህግ የበላይነትን ለማረጋገጥ የላቀ ፋይዳ እንዳለው ተገለጸ

የኦሮሞ ህዝብ ከጥንት ጀምሮ ሲተዳደርበት የነበረው የገዳ ስርዓት የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ትስስር ከማጠናከሩም ባሻገር የመከባበር ባህል እንድጎለብትና ህብረተሰቡ በሁለንተናዊ መልኩ መለወጥ እንዲችል መሰረት የሆነ ስርዓት መሆኑ ተገለፀ፡፡ በመጪው እሁድ የሚከበረውን የኢሬቻ በዓልን አስመልክቶ ዛሬ በቢሾፍቱ ከተማ የፓናል ውይይትና የህፃናት ሩጫ ተካሂዷል፡፡ በፓናል ውይይቱ የገዳ ስርዓትና የገዳ ስርዓትን በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የትምህርትና ባህል ተቋም/ዩኔስኮ/ ለማስዝገብ እየተደረገ ያለውን አጠቃላይ እንቅስቃሴ የሚመለከት የመወያያ ፅሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…

በኢህአዴግ እንደገና በመታደስ ዙሪያ በፌዴራል መስሪያ ቤቶች የሚገኙ የድርጅቱ የመካከለኛ አመራር አካላት የሁለት ቀናት ግምገማዊ ስልጠና መድረክ ተካሄደ

በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመስብሰቢያ አዳራሽ ከሁሉም የፌዴራል ተቋማት የተውጣጡ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች የመካከለኛ አመራር አካላት የኢህአዴግ ምክር ቤት የሀገሪቱን ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችንና ድርጅቱ አሁን ላይ ያለበትን ነባራዊ ሁኔታ በመገምገም የለያቸውን ስኬቶችንና ውስንነቶችን መሰረት በማድረግ የተላለፈውን እንደገና በጥልቀት የመታደስ ድተርጅታዊ ውሳኔ የተመለከተ የሁለት ቀናት ውይይት አካሄደዋል፡፡

ተጨማሪ ያንብቡ…