ከኢህአዴግ ምክር ቤት ፅ/ቤት ሃላፊ፣ አቶ ሬድዋን ሁሴን ጋር የተደረገ ቃለ ምልልስ፡፡
አቶ ሬድዋን፡- ባለፈው አመት የነበሩት ዋና ዋና ዕቅዶች የተጀመረውን የኢትዮጵያን ህዳሴ የማስቀጠል ስራ አንድ ምዕራፍ ተደርገው ይወሰዳሉ፡፡ የአምስት አመቱን የእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ከማሳካት አንፃር የመፈጸም አቅም መገንባትና ስራው በተቀናጀ መንገድ መፈጸም ስላለበት በድርጅት፣ በመንግስትና በተጠቃሚው ህዝብ በኩል በተደራጀ መንገድ የሚደረገው እንቅስቃሴ በሰፊው ህዝብ ጥቅም ላይ የተመሰረተ እንዲሆን ለውጡን የማስቀጠል ስራን ግምት ውስጥ ያስገባና በየደረጃው በሚገኙ አካላት የመፈፀም አቅም ግንባታ ላይ የተመሰረተ ነበር፡፡ የመፈጸም አቅም ለመገንባት ደግሞ በአቅም ግንባታ ስራው የአመራሩን አቅም መገንባት አስፈላጊ ነበር፡፡ በዚህም ከከፍተኛው አመራር ጀምሮ ሰፊ ስልጠናዎችን ለመስጠት ተሞክሯል፡፡ ቀጥሎም በመካከለኛ አመራር ደረጃ ስልጠና ለመስጠት ነበር የተሞከረው፡፡ ይኽው ስልጠና በተለያየ ደረጃ ሲሰጥ ቆይቷል፡፡ አሁንም በመሰጠት ላይ ነው፡፡ የአቅም ግንባታ ስራው ዋናው ዓላማ የህዝብ ተጠቃሚነትን መሰረት አድርጎ መንቀሳቀስ ነው፡፡ ለዚህም በአቅም ግንባታ ላይ የተመሰረተ ስልጠና ወስዶ በተገኘው የአቅም ግንባታ መሰረት መንግስትንም ህዝቡንም ማንቀሳቀስ የሚያስችል የድርጅት አቅምን መገንባት ማለት ነው፡፡
Among the top in agenda is having the new leadership in China. How do you see the ongoing congress which has attracted great attention from all over the world?
First of all, I would like to congratulate the entire leadership of the CPC for its 18th congress on behalf of the EPRDF secretariat and the leadership
የኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢህአዴግ) ለከፍተኛ አመራር በተከታታይ እየሰጠ ባለው ስልጠና ዙሪያ የኢህአዴግ የህዝብ ግንኙነት ክፍል ከክቡር አቶ በረከት ስምዖን ጋር ያደረገው ቃለ ምልልስ
አቶ በረከት - እንደሚታወቀው በኢህአዴግ በኩል የሰው ሃይሉን በተለይ የአመራሩን አቅም ለመገንባት ሁለት መሰረታዊ አቅጣጫዎችን ይከተላል፡፡ አንደኛው ስልጠና ነው፡፡ ሁለተኛው የአመራር አካላትን በተግባር ውስጥ አስገብቶ የድርጅቱንና የመንግስትን እቅድ በመፈፀም ህዝብ በማገልገል ተጠናክረው እንዲወጡ ማድረግ ነው፡፡ ይህ ከግምገማ ጋር አያይዞ የአቅም ግንባታ የማካሄዱ ስራ ነው፡፡ የአሁኑ ስልጠና ከበፊቱ ስልጠናዎች ለየት የሚያደርገው ነገር ድርጅታችን እያደገና እየሰፋ በመሄድ ላይ ያለ ድርጅት ነው፡፡ መንግስትም መዋቅሩና ተግባራቱ እየሰፋ ነው፡፡ መንግስትም ሆነ ድርጅቱ ለህዝብ መስጠት ያለባቸውን የአመራር አገልግሉት በአግባቡ እንዲወጡ ለማድረግ በተለይ የአስፈፃሚ አካላት ውስጥ የሚገኙ ከፍተኛ ሃላፊዎች በየጊዜው ስልጠናዎች ማግኘት ይኖርባቸዋል፡፡ በሀገር ውስጥ ልማትን ማረጋገጥ እና መልካም አስተዳደር የማስፈን ትግሉ እየሰፋና እየተወሳሰበ የሚሄድ ሆኗል፡፡ በአለም አቀፍ ደረጃም ሀገራችን ተወዳዳሪ እንድትሆን ይፈልጋል፡፡