የደቡብ ኢትዮትያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን 
የደቡብ ኢትዮትያ ሕዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ/ደኢህዴን/ በደርግ ውድቀት ዋዜማ ላይ የኢህአዴግ ድርጅቶች በነበሩት በሕውሀት፣ ብአዴንና፣ ኦህዴድ ውስጥ ሲታገሉ ከነበሩና ከደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች አብራክ በፈለቁ ታጋዮች ማህበር መልክ በየብሔረሰቡ የተጀመረው የተደራጀ እንቅስቃሴ በደቡብ ክልል ከተከናወነው ከፍተኛ የፖለቲካና የማደራጀት ሥራ በኃላ በ1985 ዓ/ም ብሄረሰባዊ መሰረት የነበራቸውን 21 ድርጅቶችን በማሰባሰብ የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ግንባር ደኢህዴን/ ተመሰረተ፡፡
ከአራቱ የኢህአዴግ አባል ድርጅቶች አንዱ የሆነው ደኢህዴን በየብሔራዊ አደረጃጀት የተበታተነውን ግንባር ደኢህዴግ/ን በ1995 ዓ/ም በማፍረስ ወደ አንድ ወጥ ክልላዊ ፖርቲነት የተሸጋገረ ሲሆን ንቅናቄው በክልሉ በሚገኙ በየዞኖችና ልዩ ወረዳዎች እንዲሁም በሀዋሣ ከተማ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቶችን አደራጅቷል፡፡  እስከ ገጠር ቀበሌ ድረስ የጠራ አደረጃጀትና አሰራር በመዘርጋት ፖለቲካዊና ድርጅታዊ ሥራዎችን በማከናወን ላይ ይገኛል፡፡
 
ንቅናቄው አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ አስተሣሰብና ዓላማን አንግቦ ባካሄዳቸው ትግሎች በክልሉ በህዝባዊ ምርጫ ተረክቦ ላለፉት 18 ዓመታት ንቅናቄዎችን በሚመራው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ህዝቦች ክልል ለማስፈፀም የሚንቀሣቀስ በፈቃዱ በኢህአዴግ ውስጥ የታቀፈ የኢህአዴግን ውሣኔዎች ከክልሉ ተጨባጭ ሁኔታ ጋር በማጣጣም ተግባራዊ የሚያደርግና በግንባሩ ውሣኔ የሚገዛ ነው፡፡
ንቅናቄው እስከ አሁን 7 ጉባኤዎችን ያካሄደ ሲሆን ባለፋት 18 ዓመታት መንግስታዊ ስልጣን ይዞ የክልሉንና የአገራችንን ህዳሴ እውን ለማድረግ በአብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ጎዳና በመምራት ላይ የሚገኝ ድርጅት ነው
ደኢህዴን ከ56 በላይ ብሔር ብሔረሰቦች በሚገኙበት የደቡብ ክልል ሁሉንም ብሔረሰቦች በማሰባሰብ ለብሔረሰቦች ብሄራዊና መደባዊ ጥቅሞች መረጋገጥና በፈቃዳቸው ለሚዘልቅ ክልላዊ ዴሞክራሲያዊ አንድ አብዮታዊ ዴሞክራሲያዎ አመራር እየሰጠ ይገኛል፡፡
የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች የቋንቋና የባህል ልዩነት ሣይገድባቸው በመካከላቸው ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እየገነቡ በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተው አገራዊ አንድነት ምሣሌ በመሆን እንዲጓዙ ከማድረጉም በላይ ድህነትንና ኃላቀርነትን በመፋለም ወደፊት እየገሰገሰ የሚገኝ ድርጅት ነው፡፡
 

 

የደኢህዴን ኢህአዴግ ዓላማዎች
1. የደኢህዴን/ኢህአዴግ ስትራቴጂያዊ የፖለቲካ ዓላማ
 
የደኢህዴን/ኢህአዴግ ስትራቴጂያዊ የፖለቲካ ዓላማ በህገ-መንግስቱ የተረጋገጡ የዜጎች ሰብዓዊና ዴሞክራሲያዊ መብቶች በተሟላ ሁኔታ የሚከበሩት፣ የዴሞክራሲ ባህልና ተቋሞች የሚያብቡበት፣ሕዝቡ በክልሉና በአገሪቱ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ጉዳዮች የነቃ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ተሣትፎውን የሚያረጋግጥበት፣ በሕዝቦች መብት መከበር በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ የክልሉና የኢትዮጵያ ሕዝቦች ጠንካራ አንድነት የሚጎለብትበት፣ የዳበረ ህብረ ፖርቲያዊ ዴሞክራሲያዊ ሥርዓትን መፍጠር ነው፡፡ ይህን ስትራቴጂያዊ የፖለቲካ ዓላማ ለማሣካትም የሚከተለውን የፖለቲካ ኘሮግራም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
 
     የዜጎችን መብት ማስከበር የዴሞክራሲ ተቋማትንና ባህልን ማዳበር፣
     በሰፊው ህዝብ የነቃ፣ ነፃና ዴሞክራሲያዊ ተሣትፎ ላይ የተመሰረተ የዴሞክራሲ ሥርዓት መገንባት፣
     በህዝቦች መብቶች መከበር፣ በእኩልነትና በመፈቃቀድ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ ዴሞክራሲያዊ አንድነት እንዲፈጠር መታገል፣
     ጠንካራና ዴሞክራሲያዊ የአገር መከላከያና የህግ አስከባሪ አካላት በሀገር እንዲፈጠሩ መታገል፣
 
2. የደኢህዴን/ኢህአዴግ ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ ዓላማ
የደኢህዴን ኢህአዴግ ስትራቴጂያዊ ኢኮኖሚያዊ ዓላማ ፈጣን እድገት በማረጋገጥ፣ ከዚሁ እድገት ህዝቡ በላቀ ደረጃ ተጠቃሚ የሚሆንበት ክልላችን በአገር አቀፍ አገራችን ደግሞ በዓለም አቀፋዊው የኢኮኖሚ ትስስር ውስጥ ያላት ቦታና ድርሻ ተሻሽሎ ኢኮኖሚያዊ ነፃነትዋ እየጎለበተ እንዲሄድ ለማድረግ የሚያስችል የዳበረ የነፃ ገበያ ኢኮኖሚን ለመገንባት የሚከተሉትን ነጥቦች የያዘ ስትራቴጂያዊ የኢኮኖሚ ኘሮግራም ቀርጾ ተግባራዊ ያደርጋል፡፡
 
     ገጠርንና ግብርናን ማዕከል ያደረገ የልማት አቅጣጫን መከተል፣
     የልማት ኃይሎችን በአግባቡና በቅንጅት መጠቀም፣
     በሁሉም የክልላችንና የአገራችን አካባቢዎች የተመጣጠነ እድገት እንዲኖርና የአገራችን ኢኮኖሚያዊ ነፃነት እንዲጎለብት ማድረግ፣
     ልማታችንን የሚያፋጥን የከተማ ልማት ስትራቴጂ ማውጣትና ተግባራዊ ማድረግ፣
     ፈጣን የኢንድስትሪ ልማትን ማረጋገጥ ይሆናሉ፡፡
Pages: 1  2  3